Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል አሉ።

በውይይቱ ሁለቱ ሀገራት በክህሎት ልማትና በካርበን ብድር ትብብር ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትርና ልዑካቸው ኢትዮጵያን ለመጎብኘት በመምጣታቸው ደስታቸውን ገልጸው፥ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በሲንጋፖር እየተመዘገበ ያለውን ዘላቂ እድገትና የሚታይ ለውጥ አድንቀው፥ ኢትዮጵያ ይህንን የምትከተል በመሆኑ አብረን መስራታችን ጥሩ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የተፈራረምናቸው ስምምነቶች የኢትዮጵያና የሲንጋፖርን ግንኙነት በይበልጥ የሚያጠናክሩ መሆናቸውንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

ውይይቱ ፍሬያማ መሆኑን አንስተው፥ ወደፊት የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል።

በሶስና አለማየሁ

Exit mobile version