አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡
በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ኮንቬንሽን መሠረት ኢትዮጵያ የኮፕ 32 አስተናጋጅ ሀገር ሆና መመረጧ ይታወሳል፡፡
ይህን ተክትሎም የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዚዳንት አድርጎ መመደቡን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
በዚህ መሰረትም ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከሀገር ውስጥ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከተባበሩት መንግሥታት አካላት እና ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር የኮፕ 32 ዝግጅትን የሚመሩ ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ኮንቬንሽን አባል ሀገራት ለኢትዮጵያ የማዘጋጀት ኃላፊነት በመስጠታቸው ምስጋና አቅርቧል፡፡
በቀጣይም በጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) አስተባባሪነት ከዓለም የአየር ንብረት ጥበቃ ማኅበረሰብ ጋር በቅርበት ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል፡፡

