Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኮፕ32 ለቀጣይ ትውልዶች የሚዘልቅ ትሩፋት ሊገኝበት የሚገባ ትልቅ ጉባዔ ነው – ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባዔ (ኮፕ32) ኢትዮጵያ ዓለምን የምታስተናግድበት ለቀጣይ ብዙ ትውልዶች የሚዘልቅ ዐሻራና ትሩፋት ሊገኝበት የሚገባ ትልቅ ጉባዔ ነው አሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ32 ተወካይ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)።

በትናንትናው ዕለት የኮፕ32 ተወካይ ፕሬዚዳንት መሰየምን ተከትሎ ዛሬ ጠዋት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ቁልፍ የዝግጅት ተግባራትን ለማቀናጀት የሚያስችል የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ ተደርጓል።

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት÷ ኮፕ32 ከዚህ በፊት እንደሀገር ከተዘጋጁ የተለያዩ ጉባዔዎች የተለየ፣ ሰፊ እና ወሰብሰብ ያለ የራሱ ልዩ ባህሪ ያለው ትልቅ ዓለም አቀፋዊ መድረክ ነው።

ጉባዔው እንደ ሀገራዊ እና አሕጉራዊ ፕሮጀክት ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን ገልጸው÷ ኢትዮጵያ ዓለምን የምታስተናግድበት ለቀጣይ ብዙ ትውልዶች የሚዘልቅ ዐሻራና ትሩፋት ሊገኝበት የሚገባ መሆኑን ተናግረዋል።

ጉባዔው አምስት ጉልህ የሆኑ ጉባኤዎች እንዳሉት አንስተው÷ በተጨማሪም ሌሎች በርካታ የጎንዮሽ መድረኮች፣ ዐውደ ርዕዮችና መሰል ሁነቶች እንደሚኖሩም ጠቁመዋል።

የሰመረና በርዕዩ አኳያ የተቀናጀና የተናበበ መዋቅር ኖሮን ስኬታማ ጉባዔ በማዘጋጀት በሂደቱ ሀገርን መለወጥ፣ መገንባትና ማስተዋወቅ ትልቁ ዓላማ ተደርጎ ተይዟል ነው ያሉት።

ስኬታማ ጉባዔ ማዘጋጀት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን አፍሪካ ጎልታ እንድትታይ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥና ተያይዞ ለሚመጡ ጦሶች ተጋላጭ ተደርጋ የምትታይ ብቻ ሳይሆን የመፍትሔው ማዕከልና ምንጭ በመሆን አመራር የምትሰጥ መሆኗን ለማሳየት መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version