አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ስታትስቲክስ መረጃን መሠረት ላደረገ ጠንካራ ፖሊሲ የጀርባ አጥንት ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።
19ኛው የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት የብሔራዊ ስታትስቲክስ የዳይሬክቶሬት ጀነራል ኮሚቴ ዓመታዊ ስብሰባ ‘ፍትህና ካሳ ለአፍሪካውያን እና ዘርዓ አፍሪካ’ በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስብሰባው እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ ቀርጻ ወደ ትግበራ ያስገባቻቸው የልማት ግቦችና ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተዓማኒ መረጃ ይፈልጋሉ።
ተአማኒ ስታትስቲክስ እና ልማት ተነጣጥለው እንደማይታዩ ጠቅሰው፥ ስታትስቲክስ መረጃን መሠረት ላደረገ ጠንካራ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ የጀርባ አጥንት ነው ብለዋል።
ውጥኖቹን ከግብ ለማድረስ የስታትስቲክስ ዘርፉ በሪፎርም ውስጥ ማለፉን ገልጸው፤ ዘርፉን በቴክኖሎጂ በማገዝ ኢትዮጵያ ጠንካራ ሥራ መስራቷን አመልክተዋል።
የዘርፉን ሚና ለማጎልበት ጠንካራ እና ገለልተኛ ተቋም መገንባት፣ ዘላቂ የፋይናንስ ምንጭ መፍጠር እና አኅጉራዊ ትስስርን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
እውነተኛ የስታትስቲክስ መረጃ እንደ ሀገር ሆነ እንደ አኅጉር የት እንደቆምን የማሳየት አቅም አለው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ኢትዮጵያ ዘርፉን ማዕከል ላደረጉ አኅጉራዊ ትግበራዎች ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።
በወንድሙ አዱኛ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

