አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገሪቱ የግብርናውን ዘርፍ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በበቂ ግብዓትና መካናይዜሽን በማስደገፍ እየተሰራ ነው አሉ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ።
የግብርና፣ የንግድና ቀጣናዊና ትስስር እና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴሮች በጋራ በመሆን የስንዴ ምርትና የቅባት እህሎችን ለማሳደግ ያለመ የባለድርሻ አካላት ውይይት አካሂደዋል።
አቶ አዲሱ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ እንደ ሀገር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ተኪ ምርቶችን በማብዛት የኤክስፖርት አቅምን ለማሳደግ፣ ለኢንዱስትሪዎች በቂ ምርቶችን ለማቅረብ እና ሰፊ የስራ እድልን ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።
በዚህም ባለፉት ዓመታት በተሰሩ ስራዎች አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸው÷ በስንዴ ሰብል የሚሸፈነው መሬት ከ4 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር ወደ 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር ማሳደግ ተችሏል ነው ያሉት።
በተጨማሪም 165 ሚሊየን ኩንታል የነበረው የምርት ግኝት ወደ 290 ሚሊየን ኩንታል ማሳደግ መቻሉንና ለስንዴ ግዥ ይወጣ የነበረውን 1 ቢሊየን ዶላር ማስቀረት እንደተቻለ አመላክተዋል።
በቅባትና ጥራጥሬ ምርትም ውጤታማነትን ለማሳደግ በተከናወነ ስራ ከዘርፉ ይገኝ ከነበረው 16 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ወደ 37 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።
አሁን ላይ 20 በመቶ የሚሆነው የዘይት ምርት በሀገር ውስጥ እየተመረተ እንደሚገኝ አንስተው÷ ይህንን ለማሳደግና ወደ ውጭ ለመላክ የሚያስችል አቅም ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም የእሴት ሰንሰለቱን በማጠናከርና የገበያ ትስስርን በመፍጠር ፈተናዎቹን ለማስቀረት እየተሰራ መሆኑንና ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለማቅረብ ትኩረት መሰጠቱን አብራርተዋል።
በታምራት ደለሊ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

