Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሃድ ቢዝነስ ግሩፕ ባለ 2 እና 3 እግር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ለገበያ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሃድ ቢዝነስ ግሩፕ ምቹና ወጪ ቆጣቢ የሆኑ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታውን የሚደግፉ ባለ 2 እና 3 እግር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለገበያ አቅርቧል፡

አሃድ ኤሌክትሪክ በትናንትናው ዕለት በደብረ ብርሃን ከተማ 17ኛ የመሸጫ ቦታውን አስመርቋል፡፡

የግሩፑ ም/ሥራአስኪያጅ ዘሪሁን ባካሉ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ለገበያ የቀረቡት ባለ2 እና ባለ 3 እግር የሰውና የእቃ ማመላለሻ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በአንድ ቻርጅ ከ120 እስከ 150 ኪሎ ሜትር ይጓዛሉ፡፡

ወጪን፣ ጉልበትን፣ ጊዜን እና አላስፈላጊ ብክነትን ከመቀነሳቸው በላይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸው እንደሆኑም አስረድተዋል፡፡

ተሽከርካሪዎች ከመንግስት ፖሊሲና እስትራቴጂ ጋር የተናበበ ብሎም ለአካባቢ ጥበቃ እና ኢኮኖሚ እድገት ትልቅ አበርክቶ እንዳላቸው ነው የገለጹት፡፡
አሃድ የአረንጓዴ ትራንስፖርት ቴክኖሎጂን ሲቀላቀል በዘርፉ የካበተ ልምድ ካለው የቻይናው አፍሪና ጋር በጋራ በመስራት መሆኑን አብራርተዋል።

የአሃድ ኤሌክትሪክ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ ዮናስ ተስፋዬ በበኩላቸው ÷ተሽከርካሪዎቹ ለማሽከርከር እጅግ ቀላል፣ ለተጠቃሚ ምቹ እና ድካምን የሚያቀሉ መሆናቸውን በማንሳት በገጠርም ሆነ በከተማ በቀላሉ ለተሳፋሪዎች እና እቃ ለመጫን ምቹ ሆነው የተሰሩ ናቸው ብለዋል።

አሃድ ቢዝነስ ግሩኘ ባለ 2 እግር የነዳጅ RE, TVS, BOXER እና LIFAN እንዲሁም ባለ 3 እግር የነዳጅ RE እና TVS እንዲሁም ሌሎች ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች ያስመጣ የነበረ ድርጅት መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የአሃድ ኤሌክትሪክ ማርኬቲንግ ስሥ አስኪያጅ ዳንኤል አባተ ናቸው።

አሁን ላይ ለገበያ ያቀረባቸው ባለ 2 እና 3 እግር የሕዝብና የጭነት ተሽከርካሪዎችም ገበያ ከመቅረባቸው በፊት ለሀገራችን መልክዓ ምድር ተስማሚና አዋጭ መሆናቸው በተግባር ተፈትነው መረጋገጣቸውን ጠቁመዋል።

የአሃድ ኤሌክትሪክ ማርኬቲንግ ማነጀር ዳንኤል አባተ ደግሞ ለገበያ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች ለ4 ዓመት ወይም የ60 ሺህ ኪሎ ሜትር ዋስትና ያለው ሊቲየም አይኤም ባትሪ የተገጠመላቸው መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ባትሪያቸውም በቀላሉ በቤት ውስጥ ቻርጅ መደረግ የሚችል እንደሆነ ነው ያስገነዝቡት፡፡

በደብረብርሃን ከተማ የአሃድ ኤሌክትሪክ ወኪል የየስ ስፒየር ፖርት ባለቤት አሰፋ ለገሰ እንዲሁ ቅርንጫፉ በኢትዮጵያ 17ኛው መሸጫ እንደሆነ እና ምርቱን አዲስ አበባ ከተማ ካለው የድርጅቱ ሶስት የመሸጫ ሱቆች በተጨማሪ በክልል ከተሞች በሚገኙ ወኪሎች ማግኘት እንደሚቻል ጠቅሰዋል።

በአበበ የሸዋልዑል

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version