አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ጉባዔዎችን በስኬት በማስተናገድ ተመራጭ ከተማ ሆናለች – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መዲናዋ ዓለም አቀፍ ጉባዔዎችን በስኬት በማስተናገድ ተመራጭ ሆናለች አሉ፡፡
በኢትዮጵያ የሚካሄደውን 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ አዲስ አበባ ባለፈው ዓመት ብቻ 150 ዓለም አቀፍ ጉባዔዎችን በስኬት በማስተናገድ ተመራጭ መዲና መሆኗን አረጋግጣለች፡፡
በዘንድሮው ዓመት ብቻ እስካሁን 105 የተለያዩ ኮንፈረንሶች እና ዓለም አቀፍ ሁነቶች በአዲስ አበባ ከተማ መካሄዳቸውን አመልክተዋል፡፡
ጉባዔውን የበለጠ ስኬታማ ለማድረግ የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት በዛሬው ዕለት ከመዲናዋ ባለሃብቶች እና የንግዱ ማሕበረሰብ ጋር ማድረጋቸውን ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ለተካሄዱ ጉባዔዎች የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ጠንካራ ትብብር እንደነበረው ገልጸው ÷ በቀጣይ ለሚደረጉ ጉባዔዎች ግብረ ሃይል በማቋቋም የሥራ ክፍፍል መደረጉን አብራርተዋል።
የመዲናዋ ባለሃብቶችና የንግዱ ማሕበረሰብ ለሰጡት ጠቃሚ ግብዓት፣ ሐሳብና አስተያየት እንዲሁም ለወሰዱት ኃላፊነት ከንቲባዋ አመስግነዋል፡፡
በቀጣይ ቅድመ ዝግጅቶችን በመገምገም ከምን ጊዜውም የተሻለና ደማቅ ጉባዔ ለማሰናዳት በቅንጅት እንሠራለን ነው ያሉት፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

