አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 7ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲፈጸም በጸጥታና ደህንነት ተቋማት ዝግጅት ተጀምሯል አሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) የተጻፈ “የምርጫ ደህንነትና የጸጥታ ተቋማት ሚና” የተሰኘ መጽሐፍ ዛሬ ተመርቋል።
በምረቃ መርሐ ግብሩ የጦር ሃይሎች ም/ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በመንግሥት ጸጥታ ተቋማት ላይ ውጤታማ ሪፎርም መካሄዱን ገልጸዋል።
ይህ ሪፎርም የጸጥታ ተቋማት በነጻነትና በሰብዓዊ መንገድ ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ ማስቻሉን ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡
6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሁሉን አቀፍ ሆኖ እንዲፈጸም የጸጥታ ተቋማት የላቀ ሚና መጫወታቸውን አስታውሰዋል።
በቀጣይ የሚካሄደው ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሁሉን አቀፍ ሆኖ እንዲከናወን ዝግጅት መጀመሩን ገልጸዋል።
ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባትና የመንግሥት ሥልጣን ለመያዝ የሚቻለው በምርጫ ብቻ መሆኑ ግድ የሆነበት ጊ ዜ ላይ እንገኛለን ማለታቸውን ኢዜአ ነው የዘገበው፡፡
ዓለም የደረሰበትን የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት፣ የምርጫ አስተዳደር ሥርዓት እና ያንን ሊያናጉ የሚችሉ የአሰራር ግድፈቶችን የሚያርምና የሚቆጣጠር ሥርዓት አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል።
በቀጣይ የሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲፈጸም የፀጥታ ተቋማት ሚና የላቀ እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

