Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በባህርዳር ሰባት አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ስራ ጀምረዋል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በባህርዳር ከተማ በ2018 በጀት ዓመት ብቻ ሰባት አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ስራ መጀመራቸው ተመላከተ።

የአምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ አማካሪ ኮሚቴ በከተማዋ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን የስራ እንቅስቃሴ እየጎበኘ ነው።

ጉብኝቱ የአማካሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ አምባሳደር ግርማ ብሩ የተመራ ሲሆን፤ የአማራ ክልል ርዕሰ መስዳድር አረጋ ከበደ ተገኝተዋል።

እንዲሁም የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፣ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጉብኝቱ ላይ ተሳትፈዋል።

በጉብኝቱ ወቅት እንደተገለጸው፤ ባህርዳር ከተማ ከ273 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች አሏት።

በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ ሰባት አዲዲስ ኢንዱስትሪዎች በከተማዋ ስራ የጀመሩ ሲሆን፤ 42 ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ወደ ስራ ለመግባት ማሽን በመትከል ላይ እንደሚገኙ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።

በዓለምሰገድ አሳዬ

 

Exit mobile version