አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የ’ባይቲንግ’ የሳይበር ጥቃት ለመከላከል ሊተገበሩ የሚገባቸው ሚገቡ 5 ዋና ዋና የጥንቃቄ ርምጃዎች።
- “ነፃ” የሚሉ ማባበያዎችን መጠራጠር – ጥቃት አድራሾች የሰዎችን ስሜት ለመቀስቀስ ሀሰተኛ ስጦታዎችን እንደ ማማለያ ይጠቀማሉ።
በቴሌግራም ወይም በፌስቡክ የሚመጡ “የነፃ ካርድ” ወይም “የነፃ ኢንተርኔት” ሊንኮችን በፍጹም ከመክፈት መቆጠብ፣
ያልተመዘገቡበት የሥራ ቅጥር ጋር የሚላክልዎትን መልዕክቶችን አለማመን።
- የመረጃ ማከማቻ መሣሪያዎችን (USB) በጥንቃቄ መጠቀም፦
ባለቤቱ የማይታወቅ ወይም መንገድ ላይ የተገኘ ፍላሽ ኮምፒውተር ላይ አለመስካት ውስጡ ቫይረስ ሊኖር ይችላል፣
ማንኛውንም ፍላሽ ከመክፈትዎ በፊት በጸረ-ቫይረስ (Anti-virus) መመርመር።
- ኦሪጅናል ሶፍትዌሮችን መጠቀም፡-
“ክራክ” (Cracked) የተደረጉ ወይም በነፃ የሚታደሉ ሶፍትዌሮችን አይጫኑ፤ እነዚህ አብዛኛውን ጊዜ የጥቃት መደበቂያዎች ናቸው፣
እንደ Windows_Defender ያሉ የጸረ-ቫይረስ ሶፍትዌሮችን በየጊዜው ማዘመን።
- ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (Two-Factor Authentication) መጠቀም፡-
በቴሌግራም፣ በፌስቡክ እና በኢ-ሜይል ላይ ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ ማብራት። ይህ የይለፍ ቃል ቢሰረቅ እንኳ ሌላ ሰው እንዳይገባ ይከላከላል።
- የድረ-ገጽ አድራሻዎችን (URL) መመርመር
አንድን ሊንክ ከመጫንዎ በፊት ፊደላቱን በጥንቃቄ ያንብቡ። ለምሳሌ ትክክለኛው telebirr.com ሆኖ ሳለ፣ አጥቂዎች tele-birr-free.com የሚል ተመሳሳይ የሚመስል ግን የተሳሳተ አድራሻ ሊጠቀሙ እንደሚችሉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ይመክራል።

