Fana: At a Speed of Life!

 የባይቲንግ ጥቃት ተጋላጭነት እና ጥንቃቄዎቹ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የ’ባይቲንግ’ የሳይበር ጥቃት ለመከላከል ሊተገበሩ የሚገባቸው ሚገቡ 5 ዋና ዋና የጥንቃቄ ርምጃዎች።

  1. “ነፃ” የሚሉ ማባበያዎችን መጠራጠር – ጥቃት አድራሾች የሰዎችን ስሜት ለመቀስቀስ ሀሰተኛ ስጦታዎችን እንደ ማማለያ ይጠቀማሉ።

በቴሌግራም ወይም በፌስቡክ የሚመጡ “የነፃ ካርድ” ወይም “የነፃ ኢንተርኔት” ሊንኮችን በፍጹም ከመክፈት መቆጠብ፣

ያልተመዘገቡበት የሥራ ቅጥር ጋር የሚላክልዎትን መልዕክቶችን አለማመን።

  1. የመረጃ ማከማቻ መሣሪያዎችን (USB) በጥንቃቄ መጠቀም፦

ባለቤቱ የማይታወቅ ወይም መንገድ ላይ የተገኘ ፍላሽ ኮምፒውተር ላይ አለመስካት ውስጡ ቫይረስ ሊኖር ይችላል፣

ማንኛውንም ፍላሽ ከመክፈትዎ በፊት በጸረ-ቫይረስ (Anti-virus) መመርመር።

  1. ኦሪጅናል ሶፍትዌሮችን መጠቀም፡-

“ክራክ” (Cracked) የተደረጉ ወይም በነፃ የሚታደሉ ሶፍትዌሮችን አይጫኑ፤ እነዚህ አብዛኛውን ጊዜ የጥቃት መደበቂያዎች ናቸው፣

እንደ Windows_Defender ያሉ የጸረ-ቫይረስ ሶፍትዌሮችን በየጊዜው ማዘመን።

  1. ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (Two-Factor Authentication) መጠቀም፡-

በቴሌግራም፣ በፌስቡክ እና በኢ-ሜይል ላይ ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ ማብራት። ይህ የይለፍ ቃል ቢሰረቅ እንኳ ሌላ ሰው እንዳይገባ ይከላከላል።

  1. የድረ-ገጽ አድራሻዎችን (URL) መመርመር

አንድን ሊንክ ከመጫንዎ በፊት ፊደላቱን በጥንቃቄ ያንብቡ። ለምሳሌ ትክክለኛው telebirr.com ሆኖ ሳለ፣ አጥቂዎች tele-birr-free.com የሚል ተመሳሳይ የሚመስል ግን የተሳሳተ አድራሻ ሊጠቀሙ እንደሚችሉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ይመክራል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.