Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ደህንነታቸው የተጠበቀ የዲጂታል ስርዓቶች የሚበራከቱበት ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ሉዓላዊ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ የዲጂታል ስርዓቶች የሚበራከቱበት ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብሔራዊ የዲጂታል ትራስፎርሜሽን ምክር ቤት ሊቀ መንበር ተመስገን ጥሩነህ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ይፋ አድርገዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ማጠናቀቂያ እና በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ስትራቴጂው ዜጎችን ማዕከል ያደረገ መንግሥታዊ ስርዓት የበለጠ የሚሰፋበት መሆኑን ተናግረዋል።

ስትራተጂው አካታች የዲጂታል አገልግሎቶች የሚቀርቡበት፣ ሉዓላዊ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ የዲጂታል ስርዓቶች የሚበራከቱበት ነው ብለዋል።

ከዚህም ባለፈ የውስጥ ፈጠራ የሚበረታታበት እንደሆነ ገልጸው፤ መንግሥት የዲጂታል ኢትዮጵያ መርሃ ግብርን መዘርጋቱን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የአገልግሎት አሰጣጥን፣ የህዝብ ትስስርን፣ የንግድ ስርዓትን፣ የመንግስት ተደራሽነትን፣ የፀጥታ እና ደህንነት አጠባበቅን ጨምሮ የተለያዩ አሰራሮችን ቀይሯል ነው ያሉት።

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መፅደቁን አስታውሰው፤ ስትራቴጂው በጋራ ጥረት፣ ትጋት እና ትብብር የተጀመሩ የዲጂታል ውጥኖች በፍጥነት የሚስፋፉበት መሆኑን ገልጸዋል።

እንዲሁም ተናባቢ የዲጂታል ስነ-ምህዳር የሚገነባበት፣ ዘላቂ የዲጂታል እምርታ የሚመጣበትና ሀገራዊ ትራንስፎርሜሽን የሚረጋገጥበት ማዕቀፍ ነው ብለዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version