አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ባለፉት 5 ወራት ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች ወደ ልማት ገብተዋል አለ የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ።
የቢሮው ምክትል ሃላፊና የኢንቨስትመንት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ከበደ እንዳሉት ÷ በክልሉ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ይበልጥ ለማነቃቃት በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
ባለፉት 5 ወራት 42 ባለሃብቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቁመው ÷ ወደ ሥራ ከገቡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መካከል 34ቱ በግብርና ዘርፍ መሰማራታቸውን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም አምስቱ በአገልግሎት ዘርፍ እና ሦስቱ ደግሞ በኢንዱስትሪ ዘርፍ መሰማራታቸውን ነው ያስረዱት፡፡
በፕሮጀክቶቹ ከ35 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ እድልን መፍጠር መቻሉን አቶ ተስፋዬ አመላክተዋል።
የክልሉን ሰፊ የመልማት አቅም ለመጠቀም በተከናወነ ሥራ የኢንቨስትመንት ፍሰት እየጨመረ መምጣቱን አስገንዝበዋል፡፡
በሁሉም የኢንቨስትመንት ዘርፎች ክልሉን ለማልማት ከባለሃብቱ ጋር በትብብር እንደሚሰራ ጠቅሰው ÷ በተለይም በኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሚሰማሩ አልሚዎች ቅድሚያ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
በቅድስት በርታ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

