Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኦሮሚያ ክልል የመጀመሪያ ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ ሀሰን አሊ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል የመጀመሪያ ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ ሀሰን አሊ ከ29 ዓመታት ቆይታ በኋላ በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

አቶ ሀሰን አሊ ከቤተሰቦቻቸው ጋር አዲስ አበባ ሲገቡ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዚህ ወቅት÷አቶ ሀሰን አሊ ከሶስት አስርት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገራቸው ሲገቡ አቀባበል ስላደረጉላቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

አቶ ሀሰን አሊ በኦሮሞ ሕዝብ ትግል ውስጥ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱና ክልሉ አሁን ለደረሰበት ደረጃ ሚናቸው ጉልህ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

 

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version