Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቁልቢ የቅዱስ‎ ገብርኤል ንግስ በዓል በስኬት ተጠናቅቋል – ፌደራል ፖሊስ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቁልቢ የቅዱስ‎ ገብርኤል ንግስ በዓል በስኬት ተጠናቅቋል አለ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ።

የምሥራቅ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ የኦፕሬሽን ምክትል መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ታደሰ ሲሳይ እንዳሉት፤ ‎በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በዓመት 2 ጊዜ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል ያለ ምንም ችግር ተጠናቅቋል።

በዓሉ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የፌደራልና የክልል ፀጥታ ኃይሎች በቅንጅት የተሰጠውን ግዳጅ በሚገባ መወጣት መቻላቸውን ገልጸው÷ በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ የራሳቸውን ድርሻ ያበረከቱ የቤተክርስቲያኗ አባቶችና የአካባቢውን ሕብረተሰብ አመስግነዋል።

በተጨማሪም በዓሉ በሚከበርበት አካባቢ ወንጀል በሚፈፅሙት ተከሳሾች ላይ ወዲያውኑ ውሳኔ ለመስጠት የተቋቋመው ፈጣን ጊዜያዊ ችሎት የስርቆት ወንጀል በፈፀሙ ተከሳሾች ላይ የእስር ቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉን አስረድተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version