የቁሉቢ የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በስኬት ተጠናቅቋል – ፌደራል ፖሊስ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቁሉቢ የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በስኬት ተጠናቅቋል አለ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ።
የምሥራቅ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ የኦፕሬሽን ምክትል መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ታደሰ ሲሳይ እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በዓመት 2 ጊዜ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል ያለ ምንም ችግር ተጠናቅቋል።
በዓሉ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የፌደራልና የክልል ፀጥታ ኃይሎች በቅንጅት የተሰጠውን ግዳጅ በሚገባ መወጣት መቻላቸውን ገልጸው÷ በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ የራሳቸውን ድርሻ ያበረከቱ የቤተክርስቲያኗ አባቶችና የአካባቢውን ሕብረተሰብ አመስግነዋል።
በተጨማሪም በዓሉ በሚከበርበት አካባቢ ወንጀል በሚፈፅሙት ተከሳሾች ላይ ወዲያውኑ ውሳኔ ለመስጠት የተቋቋመው ፈጣን ጊዜያዊ ችሎት የስርቆት ወንጀል በፈፀሙ ተከሳሾች ላይ የእስር ቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉን አስረድተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!