Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስኬታማነት መገናኛ ብዙሃን የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል – በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የታለመለትን ግብ እንዲያሳካ መገናኛ ብዙሃን የበኩላቸውን ሚና ሊጫወቱ ይገባል አሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ከቀናት በፊት በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል፡፡

በለጠ ሞላ (ዶ/ር) የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን አስመልክተው ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፥ ስትራቴጂው ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አስቻይ የልማት ሥራዎች የሚከናወኑበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የተገኙ ውጤቶችን መነሻ በማድረግ በተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ መሰረት ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ወደ ትግበራ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግርን ለማረጋገጥ የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት ማጎልበት ወሳኝ በመሆኑ ባለፉት አምስት ዓመታት የተሰሩ የክህሎት ልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል፡፡

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ካስቀመጣቸው ቁልፍ ጉዳዮች መካከል የዜጎች መረጃ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አንዱ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ፥ ከዚህ ጋር ተያይዞ የተቋማትን አቅም በማሳደግ ሀገራዊ መረጃዎችን የመጠበቅ ሥራ እንደሚከናወን ጠቅሰዋል፡፡

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ለማሳካት ከታቀደው ግብ አንጻር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ውጤታማ አፈጻጸም የተመዘገበው ተቋማት በባለቤትነት ስሜት ሚናቸውን በአግባቡ በመወጣታቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡

በቀጣይም ዲጂታል 2030 ስኬታማ እንዲሆን ተቋማት ይህንኑ ቁርጠኝነት በማጠናከር የሚያከናውኗቸውን ሥራዎች በዲጂታላይዜሽን እሳቤ በመቃኘት ሚናቸውን በሚገባ ሊወጡ ይገባል ነው ያሉት፡፡

መገናኛ ብዙሃን በስትራቴጂው የተቀመጡ አቅጣጫዎችንና ሀገራዊ ፋይዳውን ለሕብረተሰቡ በማስገንዘብ ለውጤታማነቱ ያላቸውን የማይተካ ሚና በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በኃይለማሪያም ተገኝ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version