Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 1 ሺህ 829 ሰዎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው 17 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 23 ሺህ 35 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 829 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 37 ሺህ 665 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።

ከዚህ ባለፈ የ17 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 637 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 377 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 13 ሺህ 913 መድረሱም ተገልጿል።

በኢትዮጵያ እስካሁን 717ሺህ 128 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸዋል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው እና የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኝ ሰዎች ቁጥር 23 ሺህ 113 ሲሆን፥ ከእነዚህም 248 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

Exit mobile version