አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማሌ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ‘ዶኦሞ’ በዓል በፓናል ውይይትና በባህላዊ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሌሞጌንቶ ከተማ ‘የዶኦሞ ብስራት ለሀገራዊ አንድነትና ዕድገት’ በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ በሚገኘው በዓል ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የማሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አልጋጋ ባልንሴ፤ የማሌ ብሔረሰብ የራሱ ቋንቋ፣ ባህላዊ የቀን አቆጣጠር ቀመር እና የአምልኮ ሥርዓት አለው ብለዋል።
በየዓመቱ ጥር 1 ቀን (ባሬ ፔቴ) የሚከበረው የዘመን መለወጫ ‘ዶኦሞ’ የተገባደደው ዓመት በምስጋና የሚሸኝበት እና ለአዲሱ ዓመት በጸሎት አቀባበል የሚደረግበት የብስራት በዓል መሆኑን ተናግረዋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ በበኩላቸው፤ ዶኦሞ የአንድነት፣ የሰላም እና የወንድማማችነት ተምሳሌት መሆኑን ገልጸዋል።
በዓሉ የማሌ ብሔረሰብን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና መንፈሳዊ እሴቶችን ከፍ ለማድረግና ታሪካዊ ቅርሶችን ለትውልድ ለማስተዋወቅ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አስገንዝበዋል።
ዶኦሞ ቂም ተይዞ የማይከበር በመሆኑ የተጣላ የሚታረቅበት የአንድነት እና የሰላም በዓል መሆኑን ማመልከታቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

