Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ግዙፉ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ..

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሥራን አስጀምረዋል፡፡
የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመገንባት ስትራቴጂ ኢትዮጵያን የወደፊቷ የአፍሪካ ግምባር ቀደም የአየር ትራንስፖርት በር የማድረግ አላማን ያነገበ ነው፡፡
የመጀመሪያው ምዕራፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ሥራ በዓመት 60 ሚሊየን ተጓዦችን የሚያስተናግድ ሲሆን÷ ሲጠናቀቅም አፍሪካን ከዓለም ቀዳሚ የአየር ትራንስፖርት መነኸሪያዎች አንዷ ያደርጋታል፡፡
የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት 110 ሚሊየን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም አለው፡፡
በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ፕሮጀክት ሲሆን÷ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትም ያጠናክራል፡፡
የንግድ እና ቱሪዝም ኮሪደሮችን የሚያሰፋና ኢትዮጵያንም ቀዳሚ የበይነ አህጉር ማዕከል የሚያደርግ ነው፡፡
ከአዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ 40 ኪሎ ሜትር አካባቢ የምትገኘው እና 1 ሺህ 910 ሜትር ከፍታ ያላት ቢሾፍቱ ለአውሮፕላኖች ሥራ የተመቸ ከባቢ አላት፡፡
ቢሾፍቱ ለአዲስ አበባ ያላት ቅርበት ከነባሩ የአየር ትራንስፖርት ምህዳር ጋር በቀላሉ የተዋሃደ አሠራር እንዲኖር ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡
Exit mobile version