Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአማራ ክልል የእናቶች ጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል የእናቶች ጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ጤና ቢሮ፡፡

የቢሮው ም/ኃላፊ አበበ ተምትሜ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ ከወሊድ ጋር በተያያዘ በክልሉ ለእናቶች የሚሰጠውን የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ለማጠናከር ትኩረት ተደርጓል፡፡

በዚህ መሰረትም ከ100 ሆስፒታሎች በተጨማሪ በ36 ጤና ጣቢያዎች የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ማስጀመር መቻሉን ተናግረዋል።

በጤና ጣቢያ ደረጃ የአልትራሳውንድ አገልግሎቶችን ለማስፋት ትኩረት መሰጠቱንና 318 ጤና ጣቢያዎች የአልትራ ሳውንድ አገልግሎት መጀመራቸውን ገልጸዋል።

ባለፉት 6 ወራት ከ305 ሺህ በላይ እናቶች በሕክምና ተቋማት የወለዱ ሲሆን÷ የጤና ክትትል ማድረግ መቻላቸውን አስረድተዋል፡፡

እናቶች በወሊድ ጊዜ ለሚያጋጥማቸው የደም መፍሰስ አደጋ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ከ40 ሺህ ዩኒት በላይ ደም መሰብሰቡንም አመልክተዋል፡፡

በደሳለኝ ቢራራ

Exit mobile version