አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጂቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ዛሬ ጠዋት ጂቡቲ ሲደርሱ ፕሬዚዳንቱ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ከፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ ጋር በጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮች፣ በቀጣናዊ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የሀገራቱን የሁለትዮሽ ትብብር በተለይም በንግድ፣ ሎጂስቲክስና የልማት ሥራዎች ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡
ይህም ለሰላምና መረጋጋት፣ የኢኮኖሚ ትስስርና የጋራ ብልጽግና ያለንን የወል ጽኑ አቋም ያመለክታል ነው ያሉት፡፡

