Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መጪውን ብልጽግና ታሳቢ በማድረግ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፏን እያዘመነች ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መጪውን የኢትዮጵያ ብልጽግና ታሳቢ በማድረግ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፏን እያዘመነች ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት “የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ” በሚል ሀሳብ ዐበይት ተቋማት አፈፃፀም የሚገመግሙበት እና ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚኖራቸውን ስትራቴጂያዊ የቅድሚያ ምልከታ የሚያደርጉበት ኮንፈረንስ ተካሂዷል።

ኮንፈረንሱን አስመልክቶ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢትዮጵያ ሪፎርም ስኬታማ እየሆነባቸው ከመጡ ዘርፎች መካከል ፋይናንስ አንዱ ነው ብለዋል።

ነባር ስብራቶችን በመጠገን፣ አሁናዊ ተግዳሮቶችን በመቋቋም እና መጪውን የኢትዮጵያ ብልጽግና ታሳቢ በማድረግ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፏን እያዘመነች ትገኛለች ነው ያሉት።

የፋይናንስ አስተዳዳርን በማዘመን፣ የፋይናንስ ተደራሽነትን በማስፋት፣ ሀብትን በበቂ ሁኔታ በማሰባሰብ እና አዳዲስ ሀገራዊ ሀብቶችን በመፍጠር ኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞዋን እያሣለጠች ነው በማለት ገልጸዋል።

Exit mobile version