Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሱርማ ወረዳ የተገነባውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀዳማዊት እመቤት ፅ/ ቤት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሱርማ ወረዳ የተገነባውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መርቀው ከፍተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕከት÷ በትምህርት ቤቱ የርክክብ ሥነሥርዓት ላይ ስንገኝ በአካባቢው የትምህርት መስክ እድገት ረገድ ዐቢይ ተግባር በመሆኑ ደስታ ይሰማናል ብለዋል።

ትምህርት ቤቱ በቀዳሚነት ከአካባቢው ለሚመጡ ተማሪዎች የአዳሪ ትምህርት ቤት በመሆን እንደሚያገለግል ገልፀዋል፡፡

ግቢው የመማሪያ እንዲሁም የማደሪያ ክፍሎች፣ በፀሃይ ኃይል የሚሰሩ በቂ ኮምፒውተሮች፣ የኮምፒውተር ላብራቶሪ፣ የንፁህ ውሃ ጉድጓድ፣ የተሟላ የምግብ ማብሰያ ክፍል፣ ቤተ መፃሕፍትና የአስተዳደር ሕንፃን አካትቶ የተገነባ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ይህ ምሉዕነት ያለው የትምህርት ከባቢ የተማሪዎችን አካዳሚያዊ ልህቀትና ደኅንነት ለማረጋገጥ ታስቦበት የተሰራ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ለወጣት ተማሪ ልጆቻችን ሁሉን አቀፍ እድገት አዲስ እድል የፈጠረ ተቋም ነው ሲሉ ገልፀዋል።

Exit mobile version