Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የገበታ ለትውልድ ደንቢ ኢኮ ሎጅን መረቁ

default

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገበታ ለትውልድ ሥራ የመጀመሪያው መዳረሻ የሆነው ደንቢ ኢኮ ሎጅ በይፋ ተመርቋል።

ደንቢ ኢኮ ሎጅ በ36 ነጥብ 7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ የጥብቅ ደን እና የተፈጥሮ ኃብት ስጦታ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገልጿል።

የሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍ ባለፉት ሰባት ዓመታት ዘላቂነትን፣ የቅርስ ኃብትን እና ለዘመናት የሚዘልቅ አለምአቀፍ ደረጃን የመጠበቅ እድል መፍጠርን በማዋሃድ ምን ያህል እንደተለወጠ ማሳያ ነው ብሏል።

የገበታ ለትውልድ ሥራ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ መዳረሻዎችን በማልማት የሀገራችንን እምቅ አቅም ለማውጣት የሚደረገው የሰፊው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ስትራቴጂ አካል ነው በማለት ገልጿል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመረው ይኽ ሥራ በስኬት ከተተገበሩት የገበታ ለሸገር እና ገበታ ለሀገር መርሃ ግብሮች የቀጠለ እና ሥራዎቹን ወደአዳዲስ አካባቢዎች የወሰደ መሆኑንም አመልክቷል።

የተፈጥሮ ውበትን፣ የባሕል ቅርስን እና ዘላቂ ልምድን በማቀናጀት የተከናወነም ሲሆን እነዚህ ሥራዎች የከተማ እና ተፈጥሯዊ መዳረሻዎችን ወደ ሳቢ የቱሪዝም ማዕከልነት የለወጡ ናቸው።

#DineForGenerations
#ገበታለትውልድ
#PMOEthiopia

Exit mobile version