አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በዛሬው ዕለት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ ለአካል ጉዳተኞች የዊልቼር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የሚመራው የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለአካል ጉዳተኞች ልዩ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።
በዛሬው ዕለትም ልጆቻቸው የአካል ጉዳት ገጥሟቸው ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ ለተቸገሩ ወላጆችና ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ለመማርም ሆነ ለመስራት ለተቸገሩ ወገኖች እገዛ የሚያደርግ የዊልቸር ድጋፍ መደረጉን የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

