Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአቪዬሽን ኤክስፖ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ተባባሪ አካላትን በአንድ መድረክ ያገናኘ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአቪዬሽን ኤክስፖ የኢትዮጵያ የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከልነት ሚናን ለማጠናከር የሀገር ውስጥ እና የውጭ ተባባሪ አካላትን በአንድ መድረክ ያገናኘ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ዛሬ የኢፌዲሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓልን በማስመልከት በተሰናዳው የአቪዬሽን ኤክስፖ 2026 መክፈቻ ላይ ተገኝቻለሁ ብለዋል።

“ወደፊት መብረር፣ የጋራ ነገን መገንባት” በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀው ኤክስፖ የአቪዬሽን ቴክኖሎጂን፣ ክህሎትን፣ ትብብርን የማሳደግና በማደግ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከልነት ሚናን ለማጠናከር የሐገር ውስጥ እና የውጭ ተባባሪ አካላትን በአንድ መድረክ ያገናኘ ነው ሲሉም አመልክተዋል።

Exit mobile version