Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለኢትዮጵያ አየር ኃይል ሰማይ ወሰን ሆኖ አያውቅም – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለኢትዮጵያ አየር ኃይል ሰማይ ወሰን ሆኖ አያውቅም፤ የጀግንነት አሻራውን የሚያሳርፍበት፣ ብቃቱን የሚለካበትና የሀገርን ኩራት የሚያውጅበት ሰፊ የመጫወቻ ሜዳው ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ÷ ለኢትዮጵያ አየር ኃይል ሰማይ ወሰን ሆኖ አያውቅም ሲሉ አውስተዋል፡፡

ለኢትዮጵያ አየር ኃይል ሰማዩ የጀግንነት አሻራውን የሚያሳርፍበት፣ ብቃቱን የሚለካበትና የሀገርን ኩራት የሚያውጅበት ሰፊ የመጫወቻ ሜዳው ነው ብለዋል፡፡

ሰማዩ የኛ ነው የሚል መርሁን በኩራት ለዘጠና ዓመታት አውጇል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን÷ 90 ከቁጥር በላይ ነው የምንለው በምክንያት እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡

ዘጠኝ አሥርት ዓመታት የታተመ የማይበገር የአየር ክልልን የማስጠበቅ ፅናት፣ በሰማይ ላይ የተጻፈ የሉዓላዊነት ታሪክ፣ ዘመን የተሻገረ የነጻነትና የአንድነት አርማ ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

Exit mobile version