Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ 480 ሺህ በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የምስክር ወረቀት ወሰዱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ 480 ሺህ በላይ በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የምስክር ወረቀት ወስደዋል አለ የከተማ አስተዳደሩ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ አዋሌ መሃመድ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ የ5 ሚሊየን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የወጣቶችን ዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን ያሳድጋል፡፡

ዜጎች ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ ክህሎት እንዲኖራቸው በማድረግ የፈጠራ አቅማቸውን ከማጠናከር አንጻር ጉልህ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የ5 ሚሊየን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መርሐ ግብር በታቀደው መሰረት እየተከናወነ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

በኢኒሼቲቩ በአሁኑ ወቅት በመዲናዋ 733 ሺህ በላይ ወጣቶች ሥልጠናውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ነው ሃላፊው የገለጹት፡

ከእነዚህ ውስጥም ከ480 ሺህ በላይ ወጣቶች ሥልጠናውን በሚገባ አጠናቅቀው የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን አስረድተዋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት ከ809 ሺህ በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ተከታትለው የምስክር ወረቀት እንዲወስዱ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

ወጣቶች የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ማሳለጥ የሚያስችለውን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና እንዲከታተሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

Exit mobile version