👉 ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኢትዮጵያ ሲሰራ የነበረው የኢኮኖሚ ሪፎርም የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራትን ለመቅረፍ ነው
👉 ግብርና መር መሆን ብቻውን የኢኮኖሚ ስብራታችንን ስለማይጠግን ብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ በመከተል ጥራት ያለው ዕድገት ለመፍጠር ተሰርቷል፤
👉 ኢትዮጵያ ላለፉት 20 ዓመታት ጤነኛ ያልሆነ ብድር በመበደሯ እና ብድሩን መክፈል ባለመቻሏ ብድር መበደር የማትችል ሀገር ሆና ነበር፤
👉 ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኢኮኖሚው ዘርፍ በኢትዮጵያ ታሪክ አመርቂ ውጤት የመጣበት ዘመን ነው፤
👉 አሁን ያለው የኢትዮጵያ ዕድገት ማንንም የሚያከራክር አይደለም፤
👉 የዛሬው ድህነት እኛ ላይ ሳያበቃ ወደ ልጆቻችን እንዳይሸጋገር መስራት አለብን፤
👉 በዓለም አቀፍ ግመታ በ2050 የዓለም ሕዝብ 9 ነጥብ 8 ቢሊየን ይደርሳል ተብሎ ይገመታል። ከዚህ ውስጥ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን የአፍሪካ ሕዝብ ነው።
👉 የሕዝብ ቁጥር በስርዓት ከተመራ እና ከተገራ ለኢኮኖሚ እድገት አይተኬ ሚና አለው።
👉 በ2035 አፍሪካ ተጨማሪ 450 ሚሊየን ለስራ ዝግጁ የሆኑ ሰዎች ወደ ዓለም የስራ ገበያ ትቀላቅላለች፤ ከአሁኑ ጋር ሲደመር 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ወጣት አፍሪካዊ ማልማት መስራት የሚችል ይሆናል።
👉 በዚህም ከዛሬ 10 ዓመት በኋላ ዓለም ለስራ ከሚፈልጋቸው ሰዎች መካከል 50 በመቶ የሚሆነው አፍሪካ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን÷ ይህንን በመረዳት ለነገ ውድድር ማዘጋጀት ይገባል።
👉 በሪፎርሙ ላይም ትውልድ ላይም አበክሮ መስራት ተችሏል።
በወንድማገኝ ፀጋዬ እና ዮናስ ጌትነት

