👉 በ2050 አብዛኛው የዓለም ሕዝብ ወደ ከተሜነት ይስፋፋል።
👉 በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማት አሁን ላይ በኢትዮጵያ በሚገኙ በርካታ ከተሞች ማስፋፋት ተችሏል።
👉 ይህ ስራ ከተሜነት እየተስፋፋ ሲሄድ ጤናማ ኑሮ የሚኖሩ፣ አካባቢያቸውን የሚወዱ፣ በሰላም ወጥተው የሚኖሩ እና በቂ አገልግሎት የሚያገኙ ዜጎች እንዲበራከቱ ያስችላል።
👉 እያደጉ ካሉ ሀገራት ከሀገር ውስጥ ምርታቸው ውስጥ ከ9 በመቶ ያላነሰ በአየር ንብረት ብክለት ችግር ምክንያት ጉዳት ያስተናግዳሉ።
👉 ይህ በልጆቻችን ላይ እንዳይደገም እና ተስማሚ ከባቢ እንዲፈጠር እየጠፋ ያለው አረንጓዴያማነት በአረንጓዴ ዐሻራ፤ እየተበላሸ ያለውን ወንዝ በወንዝ ዳር ልማት እየቀየርን እድገቱ ተፈጥሮን ሳያበላሽ ለማምጣት ሪፎርም ሲሰራ ነበር።
👉 በልጆች የትምህርት ሥርዓት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ቴክኖሎጂ፣ በአረንጓዴ ዐሻራ እና በከተሜነት በተሰሩ ስራዎች የመጣው ውጤት የሚታይ የሚጨበጥ ዓለም ዕውቅና የሰጠው ነው።
👉 ይህ ሁሉ ስራ ሲደመር የትናንት ስራ ሲደመር ልጆቻችን ቀና ብለው ከስደት ተቆጥበው በሀገራቸው በኩራት መኖር የሚችሉ ዜጎችን የማፍራት ትልም እና ፍላጎት በዕውቀት እና ዕቅድ ገብቶን እየሰራን እንዳለን ያመላክታል።
በዮናስ ጌትነት

