Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽና ማብራሪያ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉 በ2050 አብዛኛው የዓለም ሕዝብ ወደ ከተሜነት ይስፋፋል።

👉 በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማት አሁን ላይ በኢትዮጵያ በሚገኙ በርካታ ከተሞች ማስፋፋት ተችሏል።

👉 ይህ ስራ ከተሜነት እየተስፋፋ ሲሄድ ጤናማ ኑሮ የሚኖሩ፣ አካባቢያቸውን የሚወዱ፣ በሰላም ወጥተው የሚኖሩ እና በቂ አገልግሎት የሚያገኙ ዜጎች እንዲበራከቱ ያስችላል።

👉 እያደጉ ካሉ ሀገራት ከሀገር ውስጥ ምርታቸው ውስጥ ከ9 በመቶ ያላነሰ በአየር ንብረት ብክለት ችግር ምክንያት ጉዳት ያስተናግዳሉ።

👉 ይህ በልጆቻችን ላይ እንዳይደገም እና ተስማሚ ከባቢ እንዲፈጠር እየጠፋ ያለው አረንጓዴያማነት በአረንጓዴ ዐሻራ፤ እየተበላሸ ያለውን ወንዝ በወንዝ ዳር ልማት እየቀየርን እድገቱ ተፈጥሮን ሳያበላሽ ለማምጣት ሪፎርም ሲሰራ ነበር።

👉 በልጆች የትምህርት ሥርዓት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ቴክኖሎጂ፣ በአረንጓዴ ዐሻራ እና በከተሜነት በተሰሩ ስራዎች የመጣው ውጤት የሚታይ የሚጨበጥ ዓለም ዕውቅና የሰጠው ነው።

👉 ይህ ሁሉ ስራ ሲደመር የትናንት ስራ ሲደመር ልጆቻችን ቀና ብለው ከስደት ተቆጥበው በሀገራቸው በኩራት መኖር የሚችሉ ዜጎችን የማፍራት ትልም እና ፍላጎት በዕውቀት እና ዕቅድ ገብቶን እየሰራን እንዳለን ያመላክታል።

በዮናስ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.