አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የኢኮ-ቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስፋት ያከናወነቻቸው የቱሪዝም ልማት ስራዎች የሚደነቁ ናቸው አለ የተባበሩት መንግስታት የቱሪዝም ተቋም፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ዱባይ እየተካሄደ ከሚገኘው የዓለም መንግስታት የምክክር ጉባዔ ጎን ለጎን ከተቋሙ ዋና ጸሃፊ ሸይኻ አል ነዋይስ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በቱሪዝም የአቅም ግንባታ፣ በዘላቂ ልማትና ዘርፉን በፋይናንስ መደገፍ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ዋና ጸሃፊዋ በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያ የኢኮ-ቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስፋት ያከናወነቻቸውን የቱሪዝም ልማት ስራዎች አድንቀዋል፡፡
በውይይቱ ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ተገኝተዋል፡፡

