አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና መስራች አማን ፍስሃጽዮን ሕልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ኀዘን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የኀዘን መልዕክት÷ የኢቢኤስ ቴሌቪዥን መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አማን ፍስሃጽዮን በማረፉ ኀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል፡፡
አማን ለኢትዮጵያ የግል ሚዲያ ዕድገት ወሳኝ ሚና ከነበራቸው አንዱ ነው በማለት አስታውሰዋል።
ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ባለፈች ጊዜ ሁሉ የሚጠበቅበትን አድርጓል ነው ያሉት፡፡

