Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሁለተኛውን የጣሊያን-አፍሪካ ጉባዔ በጋራ በምናስተናግድበት በዚህ ወቅት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጡ ስል ታላቅ ደስታ ይሰማኛል ብለዋል።

‎አጋጣሚው ዲፕሎማሲያዊ ስብሰባ ብቻ እንዳልሆነ ገልጸው፤ በጣሊያንና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለው ጠንካራ አጋርነት ማሳያ እንደሆነ አንስተዋል።

ይህም አጋርነት በመከባበር፤ በጋራ ኃላፊነትና ለዘላቂ ዕድገት ባለን የጋራ ርዕይ ላይ የተመሠረተ ነው ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ ጉብኝት በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በኢነርጂ፣ በመሠረተ ልማት፣ በግብርና እና በፈጠራ ዘርፎች የቀጠለውን ትብብራችን ለማጠናከር ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Exit mobile version