Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ የአፍሪካን ሁለንተናዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር በቁርጠኝነት እየሰራች ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካን ሁለንተናዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር በቁርጠኝነት እየሰራች ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡
39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በጉባዔው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እንኳን የሰው ዘር መገኛ ወደሆነችው ኢትዮጵያ በደህና መጣችሁ ብለዋል።
በአፍሪካ ዘላቂ ልማትና እድገትን ለማረጋገጥ በቅንጅትና በትብብር መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
አሁን ላይ የአፍሪካ ሀገራት አመርቂ እድገት እያስመዘገቡ እንደሚገኙ አውስተው፥ የተጀመረውን ዕድገት ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የሀገራቱን ሁለንተናዊ ትስስርን ይበልጥ ለማሰለጥ በዘርፉ የጀመረችው ኢንቨስትመንት ተጠናክሮ መቀጠሉን ነው ያመለከቱት።
ለአብነትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሕዝቦችን ከማገናኘት ባለፈ የገበያ ትሰስርን በመፍጠር የኢኮኖሚ እድገትን እያጠናከረ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
ሥራውን ይበልጥ ለማሳደግም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ግዙፍ የሆነውን አውሮፕላን ማረፊያ በቢሾፍቱ እየገነባች ትገኛለች ነው ያሉት።
ከዚህ ባለፈም ኢትዮ ቴሌኮም የአፍሪካን ትስስር ለማጠናከር የበኩሉን ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
በመላኩ ገድፍ
Exit mobile version