Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ የውስጥ ደዌ ሕክምና ተደራሽነትን ለማጠናከር…

በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቱሉ ዲምቱ አካባቢ የውስጥ ደዌ ሕክምና አገልግሎት ተደራሽነትን ይበልጥ የሚያጠናክር  የውስጥ ደዌ ሕክምና ማዕከል ተመርቋል፡፡

የአይ ሲ ኤም ሲ አጠቃላይ ሆስፒታል ያስመረቀው የውስጥ ደዌ ሕክምና ማዕከል ለኮዬ ፈጨ፣ ቱሉ ዲምቱ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ለሸገር ከተማና ለአጎራባች የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ብሎም ለመላው የሀገሪቱ ሕዝቦች ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት መስጠት ያስችላል፡፡

አዲሱ የውስጥ ደዌ የሕክምና ማዕከል የዘርፉን ሕክምና ተደራሽነትን ወይም የአገልግሎት ሽፋንን ለማስፋት ሚናው ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በአይ ሲ ኤም ሲ አጠቃላይ ሆስፒታል ያሉትን የሕክምና ስፔሻሊስቶች እና ዘመናዊ መሣሪያዎችን በጋራ በመጠቀም ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡

በማዕከሉ የውስጥ ደዌ ሕክምና፣ የላብራቶሪ ምርመራ፣ የራጂ እና የአልትራ ሳውንድ፣ የፋርማሲ እና ሰው ሠራሽ መተንፈሻና የነፍስ አድን መሣሪያዎች በተገጠመላቸው አምቡላንሶች ቀልጣፋ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተጠቅሷል፡፡

ሆስፒታሉ በቅርቡም የእናቶች እና የሕፃናት ማማከር እና ሕክምና አገልግሎት እንዲሁም የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ነው የተገለጸው፡፡

 

Exit mobile version