አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ ለ3ኛ ጊዜ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ ለ3ኛ ጊዜ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው እንኳን ደስ አለዎት እያልኩ የተሰማኝን ደስታ እገልጻለሁ ብለዋል።
የባርባዶስ ሕዝብ ያደረገውን ስኬታማ የዴሞክራሲ ልምምድ እንደሚያደንቁም ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ሞትሊ ለባርባዶስ ሕዝብ እድገት፣ ብልጽግና እና ዘላቂ ልማት ለሚያደርጉት ጥረት መልካም እድል እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በኢትዮጵያና ባርባዶስ መካከል ያለውን ጠንካራ ትስስርና ትብብር ለማጠናከር በጋራ እንሰራለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

