Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሉዓላዊነት ማለት የትርክት ባለቤትነትን ማረጋገጥ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሉዓላዊነት ማለት የትርክት ባለቤትነትን ማረጋገጥ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፥ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ከትናንት ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በጉባዔው መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ አፍሪካ በመርህ ደረጃ ካለው የአንድነት እሳቤ ወደ ተግባራዊ ሉዓላዊነት መሸጋገር አለባት ብለዋል፡፡

የአፍሪካን ድምፅ በማጉላት የራሷ ትርክት ባለቤት እንድትሆን ኢትዮጵያ እየሰራች እንደሆነ አንስተው፤ በአብነትም በ’ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ ኢኒሼቲቭ’ የተጀመረውን ተግባር ጠቅሰዋል።

ሉዓላዊነት ማለት እንደ ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ባሉ ኢኒሼቲቮች አፍሪካን የራሷ ትርክት ባለቤት ማድረግ ነው በማለት አስገንዝበዋል።

በዚህ ዘመን የአፍሪካ ጥንካሬ የሚመነጨው ከጠንካራ አንድነትና አስተማማኝ ህብረት መሆኑን ገልጸው፤ ሉዓላዊነት ማለት የራሳችን ትርክት ባለቤትነትን ማረጋገጥ ነው ብለዋል።

የትርክት ባለቤትነትን ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባ ገልጸው፤ አጀንዳዎችን መቅረጽ፣ ራዕይን ወደ ተግባር መለወጥ እና በዓላማ መመራት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

Exit mobile version