አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተማ በዛሬው ዕለት ገብተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ደምቢዶሎ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአካባቢው በሚኖራቸው ቆይታ በክልሉ መንግሥት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

