Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት የተፈጥሮ ኃብታችንን እንዴት ለሀገር ጥቅም ልንጠቀምበት እንደምንችል የሚያሳይ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት ፕሮጀክት የተፈጥሮ ኃብታችንን እንዴት ለሀገር እና ሕዝብ ጥቅም በኃላፊነት ልንጠቀምበት እንደምንችል የሚያሳይ አይነተኛ ምሳሌ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ በምዕራብ ወለጋ ዞን የሚገኘው ፕሮጀክቱ በመንግሥት እና የግል ኢንቨስተሮች ትብብር እየተሠራ የሚገኝ ነው ብለዋል።

ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር ፕሮጀክቱ ለትምህርት፣ የመንገድ ልማት፣ የጤና ተቋማት እና ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት ግንባታን የማነቃቃት አቅም እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ፋይዳ በአንድ የተወሰነ ብቻ ሳይሆን የአካባቢውን ማኅበረሰብ የበለጠ ለልማት በማነሳሳት ከፍ ያለ ሚናውን እንደሚያስቀጥል እምነቴ የፀና ነው ሲሉም ገልጸዋል።

የቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት ፕሮጀክት የተፈጥሮ ኃብትን እንዴት ለሀገር እና ሕዝብ ጥቅም በኃላፊነት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳይ አይነተኛ ምሳሌ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡

Exit mobile version