Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአርጆ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ልማት ዐቢይ ሚና ይጫወታል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአርጆ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ ከውጭ ሲገባ የነበረውን የተፈጨ ድንጋይ ፍላጎት በሀገር ውስጥ በማሟላት በኢትዮጵያ የዘርፉ የኢንዱስትሪ ልማት ዐቢይ ሚና ይጫወታል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ ፋብሪካው ለሲሚንቶ፣ ለብረት እና ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች አስፈላጊ ጥሬ ግብዓቶችን ያቀርባል ብለዋል።

በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃን በማረጋገጥ የኢንዱስትሪ ልማትን እንደምታሳድግ ማሳያ መሆኑን አመልክተዋል።

Exit mobile version