Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በገጠር ኮሪደር መርሐ ግብር የአርሶና አርብቶ አደሮችን ሕይወት የመቀየር ሥራ በመስፋፋት ላይ ይገኛል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

‎አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በገጠር ኮሪደር መርሐ ግብር የአርሶ እና አርብቶ አደሮችን ሕይወት የመቀየር ሥራ በመላው ሀገራችን በመስፋፋት ላይ ይገኛል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ በምስራቅ ወለጋ ዞን የመደ ጃለላ ቀበሌ የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራን መጎብኘታቸውን አስታውቀዋል።

በዚህም በገጠር ኮሪደር መርሐ ግብር የአርሶ እና አርብቶ አደሮችን ሕይወት የመቀየር ሥራ በመላው ሀገራችን በመስፋፋት ላይ ይገኛል ብለዋል።

በምስራቅ ወለጋ ዞን ላይ እየተሠራ ያለው የመደ ጃለላ ቀበሌ የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራ ዘመናዊ የፀሐይ ኃይል መጠቀሚያ፣ የባዮጋዝ ሥርዓት፣ የእንስሳት በረቶች፣ መጸዳጃ ክፍሎች እና የምድረ ግቢ አረንጓዴ ስፍራዎች ሥራን ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል።

እንዲሁም ለማኅበረሰቡ ዘላቂ እና የከበረ አኗኗርን የፈጠረ ሥራ እንደሆነ አመልክተዋል።

Exit mobile version