Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጥቅም ሳይሰጡ የቆዩ ቦታዎች ወደ ግብርና ልማት ማዕከልነት እየተቀየሩ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከዚህ ቀደም ጥቅም ሳይሰጡ የቆዩ በርካታ ቦታዎች አሁን ላይ በመስኖ ወደ ግብርና ልማት ማዕከልነት እየተቀየሩ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ በግብርናው ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት እየተከናወኑ ካሉ ሥራዎች መካከል ያሉንን የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር ውሃ ሃብቶች ለመስኖ ልማት የማዋሉ ስራ ዋነኛው ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ጥቅም ሳይሰጡ የቆዩ በርካታ ቦታዎች አሁን ላይ በመስኖ ወደ ግብርና ልማት ማዕከልነት እየተቀየሩ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ከእነዚህ መካከል የብላቴ ወንዝ የሚገኝበት አካባቢ ደግሞ ለዚህ ተጠቃሽ ነው ብለዋል፡፡

በአካባቢው የግል ባለሃብቶችን በማሳተፍ ሰፋፊ የፍራፍሬ ልማቶች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ጠቁመው ÷ ይህም የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ ያግዛል ነው ያሉት፡፡

Exit mobile version