Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከተለያዩ ሀገራት ከመጡ ስደተኛ ቤተሰቦች ጋር የኢፍጣር መርሐ ግብር አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተለያዩ ሀገራት ከመጡ ስደተኛ ቤተሰቦች ጋር የኢፍጣር መርሐ ግብር አካሂደዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ዛሬ ምሽት እንደተለመደው በረመዳን መንፈስ ከቡሩንዲ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ሶማሊያ፣ ኢራቅና ሶሪያ ከመጡ ስደተኛ ቤተሰቦች ጋር አፍጥር ታድመናል ብለዋል።

በተጨማሪም ከፍልስጤም፣ አፍጋኒስታን፣ ኤርትራ፣ የመን እና ሱዳን የመጡ ስደተኛ ቤተሰቦች በአፍጥር መርሐ ግብሩ ላይ መሳተፋቸውን ጠቅሰዋል፡፡

Exit mobile version