👉 የትግራይ ሕዝብ ከጦርነት ይልቅ ሰላምና ልማት ይገባዋል
👉 ወጣቶች በአሮጌ አስተሳሰብ ለጦርነት ከሚገፋፏቸው አካላት ራሳቸውን ሊጠብቁ ይገባል
👉 መንግሥት በትግራይ ክልል ሰላም እንዲሰፍንና ዳግም ጦርነት እንዳይከሰት ጽኑ ፍላጎት አለው
👉 ሕወሓት ከ50 ዓመት በፊት በነበረ ኋላቀር አስተሳሰብ የታሰረና ለውጥን ለመቀበል ፍላጎት የሌለው ድርጅት ነው
👉 ሕወሓት በአሮጌው መንገድ ለመጓዝ መሞከሩ ለግጭት ዳርጎታል
👉 ቆሞ ቀሩ ኃይል ኢትዮጵያ ትፈርሳለች የሚል የተሳሳተ ስጋት በመዝራት የለውጡን ኃይል እንደ ጠላት ሲመለከት ቆይቷል
👉 በኢትዮጵያ የነበረው የተሳሳተ ትርክት ዜጎች በጥርጣሬ እንዲኖሩ አድርጓል
👉 መንግሥት የትግራይ ሕዝብ ሰላም እንዲያገኝ ባንክ፣ መብራትና ቴሌኮም የመሳሰሉ አገልግሎቶችን በፍጥነት እንዲመለሱ አድርጓል
👉 ሆኖም ቆሞ ቀሩ ቡድን የፕሪቶሪያውን ስምምነት “መርጦ የመተግበር” ዝንባሌ እያሳየ ነው
👉 የሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ውሳኔ አላከበረም
👉 ድርጅቱ ለልማት የተመደበውን በጀት ለጦርነት ዝግጅትና ለታጣቂዎች ቀለብ እያዋለ ነው
👉 ይህም በትግራይ ሕዝብ ላይ ተጨማሪ መከራ እያመጣ ይገኛል
👉 በጦርነቱ ወቅት ለተፈጸሙት ጥፋቶች ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ በሆነ መንገድ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሽግግር ፍትሕ አስፈላጊ ነው
👉 ወንጀል የፈጸሙ አካላት በሕግ መጠየቅ አለባቸው
👉 በጦርነቱ ወቅት የተፈጸሙ ማናቸውም ዓይነት ጥፋቶች፣ ግድያዎችና ዘረፋዎች (በተለይም በአክሱም፣ ዓድዋና ሽሬ አካባቢዎች) የሚወገዝ ተግባር ነው
👉 መንግሥት ማንኛውንም የውጭ ኃይል ጣልቃ ገብነት አጥብቆ ይቃወማል፥ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ይሰራል

