Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኤርትራ ሠራዊት ወደ መቐለ እንዳይገባ ታክቲካዊ በሆነ መልኩ መንገድ ዘግተን ነበር – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኤርትራ ሠራዊት በገባበት ከተማ ሁሉ ጥፋቶችን ይፈጽም ስለነበር ወደ መቐለ እንዳይገባ ታክቲካዊ በሆነ መልኩ መንገድ ዘግተን ነበር አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግርኛ ቋንቋ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ÷ የሰሜን ዕዝ እንደተጠቃ የቀረው ኃይል ወደ ኤርትራ ከሄደ በኋላ የኤርትራ ሕዝብ እና ሻዕቢያ ለሠራዊታችን ያደረገው ድጋፍ የሚሞገስ ነበር ብለዋል።

ለድጋፉ ምስጋና መቅረቡንና የኤርትራ ሠራዊት የፈጸማቸው እኩይ ተግባራት መወገዛቸውን አስታውሰዋል።

የኤርትራ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ የተጠቃበትን አጋጣሚ ተጠቅሞ ወደ ትግራይ መግባቱን ጠቅሰው÷ መንግሥት በወቅቱ የውጭ ኃይልን ለመከላከል በሚያስችል ሁኔታ ላይ አልነበረም ነው ያሉት።

ስለሆነም የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ገብቶ ንጹሐን መግደሉን፣ ተቋማት መዝረፉን እንዲሁም የሲቪል እና ማሕበራዊ ተቋማትን በማውደም ከባድ ወንጀል መፈጸሙን ገልጸዋል።

በተለይም በአክሱም ከተማ በሁለት ቀናት ውስጥ በመቶ የሚቆጠሩ ወጣቶችን ጨፍጭፏል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ በዓድዋ፣ ዓዲግራትና ሽሬን ጨምሮ በከተሞች ቤት ማፍረሱን፣ ኢንዱስትሪዎች ማውደሙንና ማሽነሪዎች መዝረፉን አብራርተዋል።

በዚህም የወንጀል ድርጊቱ እንዳይፈጸም የተለያዩ የፌዴራል መንግሥት ባለስልጣናት ወደ አስመራ መላካቸውን አስታውሰው÷ በገባበት ከተማ ሁሉ ጥፋቶችን ይፈጽም ስለነበር ወደ መቐለ እንዳይገባ ታክቲካዊ በሆነ መለወኩ መንገድ ዘግተን ነበር ነው ያሉት።

በዮናስ ጌትነት

Exit mobile version