አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ላካ ቀበሌ በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖች ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች እርም የሚያወጡበት ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት (ባሌ) ተካሂዷል።
በአደባባይ በተካሄደው ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት (ባሌ) ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በአደጋው 125 ሰዎች የጠፉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የ80 ሰዎች አስከሬን ተገኝቶ ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።

