Fana: At a Speed of Life!

በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖች ቤተሰቦች እርም የሚያወጡበት ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ላካ ቀበሌ በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖች ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች እርም የሚያወጡበት ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት (ባሌ) ተካሂዷል።

በአደባባይ በተካሄደው ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት (ባሌ) ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በአደጋው 125 ሰዎች የጠፉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የ80 ሰዎች አስከሬን ተገኝቶ ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.