Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ፑቲን በጋሞ ዞን በደረሰው አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በተከሰተው የመንሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን በጋሞ ዞን በተከሰተው አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ሐዘን ለፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልዕክት÷በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የመሬት ናዳ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

በተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች ጉዳት የደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን በፍጥነት እንዲያገግሙም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡

በጋሞ ዞን የካቲት 30 እና መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ እና የመሬት ናዳ እስከ ትናንትናው ዕለት ድረስ የ81 ዜጎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version